የሪል እስቴት እና የባለድርሻ አካላት የግንኙነት መድረክ በሚል ዝግጅት ተደረገ

ድርጅታችን ውቅር ትሬዲንግ “የሪል እስቴት እና የባለድርሻ አካላት የግንኙነት መድረክ“ በሚል የካቲት 11/2015 በአዲስ አበባ ሳፋየር አዲስ ሆቴል የውይይት መድረክ አካሄደ።

የሪል እስቴት ሽያጭ፣ ግዢ፣ ማማከር እና  ሌሎች ስራዎችን ለመስራት በማሰብ በዘረፉ በተሰማሩ አባለት በመስከረም ወር 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተቋቋመው ውቅር ትሬዲንግ /የተ/የግ ማህበር ያዘጋጀው፤የሪል እስቴት እና የባለድርሻ አካላት የግንኙነት መድረክበሚል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በሪል እስቴት ኢንደስትሪው ላይ የተሰማሩ አገር በቀል እና አለም አቀፍ የሪል እስቴት አልሚዎች፣ የሪል እስቴት የሽያጭ አማካሪዎች፣ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች፣ በፋይናንስ ኢንደስትሪ የተሰማሩ ባንኮች እና ኢንሹራንሶች፣ የግንባታ እቃ አቅራቢዎች እንዲሁም አምራቾች ተሳትፈውበታል።

 

በመድረኩ ላይ በሪል እስቴት እና በፋይናንስ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያካበቱ አንጋፋ ባለሙያዎች በዘርፉ ዙሪያ የተለያዩ ጥናቶች ያቀረቡ ሲሆን  በጥናቶቹም፤ በሪል እስቴት ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችና የወደፊት ዕድሎች ምንድን ናቸው? በሚል በኢንጅነር ጌቱ ከበደ እንዲሁም፤ካፒታል ማርኬት እና የሪል እስቴት ዘርፍ እንዴት ይገናኛሉ?” በሚል ርእስ በአንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ፣ የብሩህ ፋይናንስ መስራች እና ባለቤት በሆኑት አቶ ጌታቸው ባሻወርድ ሀሳቦች ተነስተውው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

Wiqir Trading event participant
የውቅር ትዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ስራ አስኪያጅ አቶ ዘመኑ ታደሰ

በውይይቱም ላይከተነሱ አንኳር ሃሳቦቸ ውስጥ የኢቨስትመንት ፍቃድ አለማግኘት፣ ለሪል እስቴት ልማት የሚውል ቦታ በጊዜው አለማግኘት፣ በየቢሮዎቹ የሚታዩ የቢሮክራሲ ችግሮች እንዲሁም አልሚዎች በዘርፉ ላይ ያላቸው እውቀት ዝቅተኛ መሆን እንደ ክፍተት የተነሱ ሲሆን፤ የህዝብ ቁጥር እድገት፣ የከተሞች አኗኗር ዘይቤ መዘመንና የቤት ፈላጊዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደገ መምጣት ለዘርፉ እንደ መልካም አጋጣሚዎች የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም ዘርፉ ካሉበት ክፍተቶች ዋነኛው ዘመኑን የዋጀ ተግባቦት በሪል እስቴት ሽያጭ ባለሙያዎች ዘንድ አለመኖርሩ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በጥናቶች መሰረት ከ82 በመቶ በላይ ሽያጮች የሚከሽፉት በቢዝነስ ኮሙኒኬሽን ልከኛ አለመሆን መሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

በዝግጅቱ ማጠቃለያም በሪል እስቴት ሽያጭ ዘረፍ የሚታየውን ዘረፈ ብዙ ችግሮች ለመግታት ብሎም ለማስቅርት የሪል እስቴት ሽያጭ ባለሙያዎች በማሕበር ተደራጅተው መስራት ቢችሉ በዘርፉ የተሻለ ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ የተጠቆመ ሲሆን ውቅር ትሬዲንግም ይህንን ሃሳብ አውን ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ለዚህም የዘረፎ ተዋንያን አብረዎት እንዲሰሩ እና አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደረጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.

Scroll to Top